Vision and Mission

ራዕይ (ተልዕኮ፣ራዕይ፣እሴቶች፣የሥልጣንና ኃላፊነትወሰንትንተና) 

ተልዕኮ

የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በመቋቋም በራስ አቅም ምላሽ የሚሰጥ እና ከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰብ በዘላቂ የልማት አማራጮች እንዲሳተፉ በማገዝ የምግብ ዋስትና በቤተሰብ ደረጃ እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡

 ራዕይ

ለአደጋዎች ምላሽ የሚሰጥ፣ ለአደጋ የማይበገር እና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትና ያረጋገጠ ህዝብና ክልል ማየት፡፡

ዓላማ

ኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲና ስትራቴጂ በተሟላ መልኩ በመተግበር አደጋን የመቋቋም እንዲሁም በራስ አቅምአደጋ ክስተት ምላሽ ለመስጠት አቅም በመገንባትና የምግብ ዋስትና ፕሮግራሞችን በማስተባበርና መተግበር የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ማረጋገጥ ነው፡፡

እሴቶች

  • ቅድሚያ ሕይወትን ማትርፍ፤
  • ሰብአዊነት፤
  • ፈጣንና ውጤታማ ምላሽ መስጠት፤
  • የአደጋ ተጎጂዎችን ማክበር፤
  • አለማዳላት፤
  • ተደራሽነት፤
  • ተጠያቂነት፤
  • ቅንጅታዊ አሰራር፤
  • ሀብት ብክነትና ብልሹ አሰራርን መከላከል ናቸው።