About Us

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ተቋም በሀገሪቱ የፌደራሊዝም መዋቅር እና በተሻሻለው የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ መሠረት የክልሉን ማህበረሰብ ከአደጋዎች የመጠበቅ እና የመከላከል ሙሉ ኃላፊነት የተሰጠው የመንግሥት አካል ነው። ተቋማችን ከተለመደው የአደጋ ጊዜ ድንገተኛ ዕርዳታ አሰጣጥ ባለፈ፣ አደጋን አስቀድሞ መከላከል እና የአደጋ ስጋትን መቀነስ (Disaster Risk Reduction) ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል።